ቴሌድራይቭ
 • የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በስልካቸው ያስቀመጧቸውን የተለያዩ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ የፅሁፍ መልዕክት እና የስልክ አድራሻዎች ለማከማቸት ይረዳል፡፡ ይህም ደንበኞች ስልካቸው ቢሰረቅ፣ ቢጠፋ ወይም ቀፎ ቢቀይሩ የተቀመጡትን መረጃዎች መልሰው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

 

What-is-Cloud-Storage

ሦስት ፓኬጆች አሉ


25 ጂቢእና 100 ጂቢ

 • መረጃዎችን ከስር ከስር በምትክነት ያስቀምጣል
 • ፎቶዎች ያላቸውን የፎቶ ጥራት እንደያዙ ይቀመጣሉ
 • የሞባይላችን ማህደር (storage) እንዳይሞላ ያደርጋል
 • አልበሞችን በራሱ በመፍጠር የሚያስቀምጥ እንዲሁም የዕለቱ ምርጥ ፎቶ በመምረጥ ያሳያል
 • ፎቶዎችን በስም እና በቦታ ለመፈለግ እንዲሁም የደንበኞችን ምርጥ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡
 • መረጃዎችን ወደሌላ በሊንክ፣ በኢሜል እና በመረጧቸው ማህበራዊ መተግበሪያዎች ለመላክ ያስችላል
 • የቤተሰብ የግል ማህደር ያለው
 • የተቀናጁ አልበሞች ያሉት
 • የስልክ አድራሻዎችን እና የፅሁፍ መልዕክት መረጃዎችን ያስቀምጣል


ያልተገደበ ጥቅል

ያልተገደበ ጥቅል የባለ 25 ጊ.ባ እና 100 ጊ.ባ ጥቅል የሚሰጡትን አገልግሎት ጨምሮ ከታች የተዘረዘሩትንም አካቶ ይይዛል፡፡

 • ያልተገደበ የክላውድ ማከማቻ
 • የፎቶ ኤዲተር እንዲሁም ስቲከሮች እና ማጥሪያዎች ያሉት
 • በአንድ የተቀነባበሩ የተለያዩ ፎቶዎችን ለማጋራት እንዲሁም ከሙዚቃ ጋር ለማቀናጀት
 • ፎቶዎችን በስያሜያቸው እና በሰዎች መልክ በመለየት የሚያስቀምጥ እንዲሁም የሚፈልግ
 • ቫይረስ መከላከያ ያለው
 • አገልግሎቱን እንደምንጠቀምበት መሳሪያ ቪዲዮዎች የተሻለ ጥራት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

ታሪፍ

የጥቅል አይነት ወርሃዊ ክፍያ በብርየቆይታ ጊዜ
25 ጊ.ባ3030 ቀናት
100 ጊ.ባ6530 ቀናት
ያልተገደበ ማከማቻ30030 ቀናት

ማስታወሻ

 • ደንበኞች 30 ቀናት የሙከራ ጊዜ ስላላቸው ያለገደብ አገልግሎቱን በመጠቀም መሞከር ይችላሉ፡፡
 • 30 ቀን የሙከራ ጊዜ የሚቀርበው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ከታች የተጠቀሱትን የእንግሊዘኛ ፊደላት ወደ 615

 • ለባለ 25 ጊ.ባ A ይጠቀሙ፡፡
 • ለባለ 100 ጊ.ባ B ይጠቀሙ፡፡
 • ያልተገደበ ጥቅል ለመመዝገብ C ይጠቀሙ፡፡

ከታች የተጠቀሱትን የእንግሊዘኛ ፊደላት ወደ 615

 • ለባለ 25 ጊ.በ StopA ብለው ይላኩ
 • ለባለ 100 ጊ.ባ StopB ብለው ይላኩ
 • ያልተገደበ ጥቅል ለማቋረጥ StopC ይጠቀሙ፡፡
 • መጀመሪያ የተመዘገቡትን ጥቅል በማቋረጥ መቀየር የፈለጉበትን አዲሱን የጥቅል መመዝገቢያ መለያ ፊደል ወደ 615 ይላኩ፡፡