የሞባይል የአየር ሰዓት እና ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት

 • የሞባይል የአየር ሰዓት ክሬዲት አገልግሎት

አገልግሎቱ ለቅድመ ክፍያ የሞባይል ደንበኞች የሞባይል አየር ሰዓትን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በብድር  እንዲያገኙ ያስችላል።

 • የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት

ለቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኞች የሞባይል ድምጽ ወይም የዳታ ጥቅሎችን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በብድር  እንዲያገኙ ያስችላል።

የሞባይል የአየር ሰዓት እና የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ሁኔታዎች:

 • ያለዎት ቀሪ ሂሳብ ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜ
 • የአየር ሰዓት መሙያ አማራጭ በአቅራቢያዎ በማይገኝበት ጊዜ ወይም
 • የአየር ሰዓት መሙያ ገንዘብ ለጊዜው በማያገኙበት ጊዜ 

የሞባይል የአየር ሰዓት እና የጥቅል ክሬዲት አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ ደንበኞች

 • የአገልገሎት ጊዜው ያላለፈ የቅድመ ክፍያ የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች
 • የአገልግሎት ቁጥራቸው ያልተቋረጠ ወይም በተለያየ ምክንያት ያልተዘጋ
 • በፊት የወሰዱትን የአየር ሰዓት ብድር ሙሉ በሙሉ የከፈሉ
 • ለሦስት ወራት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በደንበኝነት የቆዩ  ደንበኞች እና በወር በትንሹ የ15 ብር የአየር ሰዓት የሚሞሉ

የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት

የዳታ ጥቅል ክሬዲት

ዕለታዊ

የዳታ ጥቅል ክሬዲት
 • 75 ሜ.ባ በ5 ብር
 • 200 ሜ.ባ. በ12 ብር

ሣምንታዊ

የዳታ ጥቅል ክሬዲት
 • 600 ሜ.ባ. በ38 ብር
 • 1 ጊ.ባ በ56 ብር

ወርሀዊ

የዳታ ጥቅል ክሬዲት
 • 1 ጊ.ባ. በ60 ብር
 • 2 ጊ.ባ. በ105 ብር

የድምፅ ጥቅል ክሬዲት

ዕለታዊ

የድምፅ ጥቅል ክሬዲት
 • 20 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ5 ብር
 • 45 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ10 ብር
 •  

ሣምንታዊ

የድምፅ ጥቅል ክሬዲት
 • 70 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ15 ብር
 • 130 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ25 ብር
 •  

ወርሃዊ

የድምፅ ጥቅልክሬዲት
 • 185 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ50 ብር
 • 375 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ95 ብር
 •  

የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሁኔታዎች


በሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚነት የቆይታ ጊዜ ያለፉት 3 ወራት የአየር ሰዓት ፍጆታ
መጠቀም የሚችሉት የዳታ እና የድምፅ ጥቅል ክሬዲት
ዳታ (በሜ.ባ)
ድምፅ (በደቂቃ)

ቢያንስ 3 ወራት
>= 15 75 20
>= 25 75 ወይም 200 20 ወይም 45
>= 60 75፣ 200 ወይም 600 20፣ 45 ወይም 70
>= 100
75፣ 200፣ 600 ወይም 1ጊ.ባ (ሳምንታዊ)
20፣ 45፣ 70 ወይም 130
>= 200 75, 200,600, 1ጊ.ባ (ሳምንታዊ/ወርሃዊ) 20፣ 45፣ 70፣ 130 ወይም 185
>= 400 75,200 ,600 ,1 ጊ.ባ. (ሳምንታዊ/ወርሃዊ) ወይም 2 ጊ.ባ 20፣ 45፣ 70፣ 130፣ 186 ወይም 375

የሞባይል የአየር ሰዓት አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሁኔታዎች

ተመዝግበው በደንበኝነት የሚጠበቅብዎት ቆይታ ጊዜ በወር መሙላት የሚጠበቅብዎት አማካኝ የገንዘብ መጠን በብር መጠቀም የሚችሉት የድምፅ ጥቅል ክሬዲት
ቢያንስ 3 ወራት ≥15 5
≥25 5፣10
≥60 5፣10፣15
≥100 5፣10፣15፣25
≥200 5፣10፣15፣25፣50
≥400 5፣10፣15፣25፣50፣100

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

 • የአየር ሰዓት ክሬዲት የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሞባይል የአየር ሰዓት በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በክሬዲት እንዲሞሉ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

አገልግሎቱን ለማግኘት እባክዎ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ

 • የሚፈልጉትን የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት A ፣ L ፣ ወይም C ብለው ወደ 810 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይላኩ፡፡ ከዚያም የተፈለገውን የሞባይል ጥቅል ክሬዲት ለማግኘት ዝርዝሩን ይከተሉ።
 • በአጭር ቁጥር *810# ላይ ይደውሉ እና የሚፈለገውን የጥቅል ክሬዲት ለማግኘት ቀጥሎ የሚመጣውን ትዕዛዝ ይከተሉ

 • የአየር ሰዓት እና
 • የጥቅል ክሬዲት አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

 • አዎ፣ የአየር ሰዓት ቀሪ ሂሳብ ብቻ ማስተላለፍ ይችላሉ።

 • የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኞች የሞባይል ድምጽ ወይም የዳታ ጥቅሎችን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በክሬዲት በቀላሉ እንዲገዙ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

 • በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ቢያንስ ለሶስት ወራት የቆዩ የቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኛ መሆን እንዲሁም በወር ቢያንስ የ15 ብር የአየር ሰዓት መሙላት።·       
 • አገልግሎቱ ያልተቋረጠ የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ደንበኛ መሆን
 • በአገልግሎት ጊዜ ማነስ ምክንያት በተቋረጠ፣ በጥፋተኝነት በተመዘገበ ወይም የአገልግሎት ጊዜው ባለፈ የሞባይል ቁጥር የክሬዲት አገልግሎቱን ማግኘት አይችሉም፡፡
 • ቀደም ሲል የወሰዱትን የክሬዲት መጠን ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ማጠናቀቅ

 • *810# ይደውሉ ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት A፣ L፣ C ብለው ወደ 810 ይላኩ።
 • ለእርዳታ ከዝርዝሩ 5 ቁጥርን ይጠቀሙ፡፡·        
 • አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ፡፡
 • የማሳወቂያ መልዕክት ይደርስዎታል።

 • በቀጣይ የአየር ሰዓት ሲሞሉ ወይም ከሌሎች ደንበኞች የአየር ሰዓት ሲላክልዎ መክፈል የሚጠበቅብዎ የሂሳብ መጠን እንዲቆረጥ ይደረጋል፡፡ የተሞላው የገንዘብ መጠን የክሬዲት መጠኑን ለመክፈል በቂ ካልሆነ፣ ክሬዲትዎን ሙሉ በሙሉ እስኪሸፈን በቀጣይነት ከሚሞሏቸው ላይ ተጨማሪ መጠን ይቀንሳል።

 • የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም - የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ ለአየር ሰዓት/ጥቅል ግዢ የሚውል ከ1 እስከ 250 ብር የሚደርስ የክሬዲት መጠን ማግኘት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ እባክዎን https://www.ethiotelecom.et/telebirr/buy-airtime/ ይጎብኙ
 • በአጭር ቁጥር - *810# በመደወል መመሪያዎቹን ይከተሉ ወይም
 • በአጭር የጽሑፍ መልዕክት - A፣ L፣ ወይም C ብለው ወደ 810 የፅሁፍ መልዕክት በመላክ መመሪያዎቹን ይከተሉ

 • በቀጣይ የአየር ሰዓት ሲሞሉ ወይም ከሦስተኛ ወገን የአየር ሰዓት ሲላክልዎ 10 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ።

 • በአጭር ቁጥር - *810# ይደውሉ --> ለእርዳታ 5 ቁጥርን ይምረጡ፣ ያለብዎትን የዕዳ ቀሪ ሂሳብ ለማረጋገጥ 2 ቁጥርን ያስገቡ። ወይም
 • በአጭር ጽሑፍ መልዕክት - A፣ L፣ ወይም C ብለው ወደ 810 መልዕክት ይላኩ --> ለእርዳታ 5 ቁጥርን ይምረጡ፣ የዕዳ ቀሪ ሂሳብን ለማረጋገጥ 2 ቁጥርን ይጠቀሙ።

 • አይችሉም፤ በመጀመሪያ የሚጠበቅብዎትን የክሬዲት መጠን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይጠበቅብዎታል።