ስለ ኢትዮ ቴሌኮም
ስለ ኢትዮቴሌኮም
We Are Africa’s Pioneer Telecom Provider, Offering Reliable Connectivity, Advanced Technology, And Financial Services To Simplify Life As We Drive Ethiopia’s Digital Transformation And Empower Communities With Innovative Solutions.
አጭር ታሪካዊ ዳራ
የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የተጀመረው በዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት በ1886 ዓ.ም. ከሐረር ከተማ ወደ ሐገሪቷ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ በተዘረጋው የቴሌፎን እና ቴሌግራፍ መስመር አማካኝነት ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ የስልክ መገናኛ መስመሮች ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በሁሉም አቅጣጫዎች እየተስፋፉ በመሄዳቸው በርካታ የአገሪቷ ዋና ዋና ከተሞች በኦፕሬተሮች አማካይነት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም አመሠራረት
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት ከ1998-2002 ዓ.ም. የተነደፈውን የአምስት ዓመት እቅድ በማስቀጠል እንዲሁም ጥረቱን በትምህርት፣ በጤናና በግብርና ላይ ትኩረት ከመስጠት ባሻገር የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ ኃይል መሆኑን በመገንዘብና አገልግሎቱን ለማሻሻል በመወሰን የሀገራችንን ቀጣይ እድገት ለማገዝ ካለው ፍላጎት አኳያ ኢትዮ ቴሌኮም ሕዳር 21 ቀን 2003 ዓ.ም በአዲስ ስያሜና በአዲስ መልክ እንዲመሠረት ተደርጓል፡፡
መዋቅራዊ አደረጃጀት (በተለያዩ ጊዚያት ከተሰጡ አዳዲስ ስያሜዎች ጋር)
- 1886 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የቴሌፎንና የቴሌግራፍ ማዕከላዊ አስተዳደር
- 1900 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የፖስታ፣ ቴሌግራፍ እና ቴሌፎን ማዕከላዊ ቢሮ
- 1903 ዓ.ም፡- የፖስታ፣ የቴሌግራፍ እና ቴሌፎን ሚኒስቴር (ፖቴቴ)
- 1945 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ
(የድርጅቱን የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት የሥራ መደቦች በወጣት ኢትዮጵያዊያን የመተካት መርሐ ግብር በ1960 ዓ.ም ተከናውኖ ተጠናቀቀ) ፤በተለያዩ ጊዚያት የተሰጡ አዳዲስ ስያሜዎችም የሚከተሉት ናቸው፡-
- 1967 ዓ.ም:- የሶሻሊስት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ድርጅት
- 1989 ዓ.ም:- የኢትጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን
- 2003 ዓ.ም:- ኢትዮ ቴሌኮም
Transition to Ethio telecom
Ethio telecom has got its current status since 29th November 2010 as a part of Ethiopia’s 2005/06 – 2009/10 GTP following the federal government’s decision to focus on improving telecom services, taking them as key to national development. Consequently, the country’s telecom infrastructure and services have been transformed to world-class standards to facilitate the development of the country with a great paradigm shift in the improvement of the sector.
የቴክኖሎጂ ዕድገት
የ5G ኔትወርክ በይፋ አገልግሎት ማስጀመር
በአዲስ ተስፋ እና እይታ ወደ አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት እና አኗኗር የሚያሸጋግረን፣ ለማህበረሰባችን በርካታ ትሩፋቶችን የሚያበረክተው እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን የሚያቀላጥፈውን የዘመናችን የመጨረሻውን የ5G ኔትወርክ ለህዝባችን በአዲስ ዓመት ስጦታነት ማበርከታችንን አብስረናል!
20235G የሞባይል ቴክኖሎጂ
ኩባንያችን ይህንን ቴክኖሎጂ በሀገራችን ዋና ከተማ እንዲሁም የዓለም አቀፍና አህጉራዊ ዲፕሎማቲክ ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ እውን ማድረጉ ተመራጭ የቴሌኮም ኦፕሬተር ነው፡፡
2022ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት
ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በ2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት ጀመረ
2020የምድር ሳተላይት ጣቢያ
- በሱሉልታ የምድርሳተላይት ጣቢያ አማካኝነት ዓለምአቀፍግንኙነትተጀመረ
በሦስት የተለያዩ አቅጣጫዎች የተተከሉ ጣቢያዎች
- በ1971 ዓ.ም: - ትልቁና 32 ሜትር ሬዲየስ ስፋት ዲሽ ያለው የሱሉልታ የምድር ሳተላይት መገናኛ አውታር ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
- በ1980 ዓ.ም: - ሁለተኛውና 13 ሜትር ሬዲየስ ስፋት ዲሽ ያለው የሱሉልታ የምድር ሳተላይት መገናኛ አውታር ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
- በ1993 ዓ.ም: - ሦስተኛውና 3 ሜትር ሬዲየስ ስፋት ዲሽ ያለው የሱሉልታ ባለዲጂታል የምድር ሳተላይት መገናኛ አውታር ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ::
የዓለም አቀፍ እና አገር ውስጥ የሬዲዮ ጣቢያ አገልግሎቶች
ለዓለም አቀፍ እና አገር ውስጥ መገናኛ አገልግሎቶች የሚውሉ የሬዲዮ ጣቢያዎች በ1944 ዓ.ም እንዲቋቋሙ ተደርጎ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ::
1952
Our company's Vision, Mission, and core values
የዚህ ስትራቴጂ ለውጥ ማዕከል የሆነው የተሻሻለው የድርጅታችን ማንነት ሲሆን እነዚህ መሠረታዊ የኩባንያችን ይዘትና ማንነት የሚገልጹ ወሳኝ ነጥቦች እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡
ራዕይ
ለዘመነች እና የዲጂታል ልዕልናን ለተጎናጸፈች ኢትዮጵያ እና ባሻገር መሪ የለውጥ አንቀሳቃሽ ኃይል መሆን
ተልዕኮ
ህይወትን ማቅለል እና የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር እና ከዚህም ባሻገር አስተማማኝ የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶችን፣ ፈጠራ ያላቸው የዲጂታል መፍትሄዎችን እና እንከን የለሽ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ማህበረሰቦችን፣ የንግድ ድርጅቶችን እና ሀገራትን ከመሠረታዊ ግንኙነት ባሻገር ማብቃት
እሴቶች
- ሰው ተኮር
- አብሮነት እና ትብብር
- ቅንነት እና ታማኝነት
- ፈጠራ
- የላቀ ብቃት
- ማህበራዊ ኃላፊነት የሚሰማው እና በጎ ተፅዕኖ መር