ግብር፣ ለሀገር ክብር!
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ኩባንያችን ዓመታዊ ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ በ2017 በጀት ዓመት 37.5 ቢሊዮን ብር በመክፈል በአንደኛ ደረጃ የፕላቲኒየም ታማኝ ግብር ከፋይነት እንዲሁም ላለፉት ተከታታይ 5 ዓመታት ግብርን በግንባር ቀደምነት በመክፈል ልዩ ተሸላሚ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው::
ይህም የላቀ አፈጻጸም ሊመዘገብ የቻለው ኩባንያችን በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የቢዝነስ አማራጮችን በመተግበር በተለይም መጠነ ሰፊ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያዎችን በማከናወን፣ የተለያዩ የዲጂታል ሶሉሽኖችና አገልግሎቶችን በማቅረብ እንዲሁም የአገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞቻችን መጨመር ጋር ተያይዞ ገቢያችንን ማሳደግ በመቻላችን ነው፡፡
ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ ባሻገር የማህበረሰባችንን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት በማቅረብ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ ስኬት ግንባር ቀደም ሚናው ጎን ለጎን ባለፉት 7 ዓመታት ከ157.5 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በታማኝነት በመክፈል የምንጊዜም የሃገር አለኝታና ኩራትነቱን አረጋግጧል።
ክቡራን ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን፤ ለማህበረሰባችን ህይወት መሻሻል እና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲሁም ለሀገር ግንባታ የበኩላችንን እንድናበረክት አብሮነታችሁ ስላልተለየን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በቀጣይም የሶስት ዓመት ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂያችን የኢትዮጵያን የዲጂታል ልዕልና ማጎናጸፍ እና ከዚያም ባሻገር ራዕያችንን ከማሳካት ጎን ለጎን ግብርን በታማኝነት በመክፈል ለዜጎች ተጠቃሚነትና ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት እንደምንተጋ በድጋሚ እናረጋግጣለን።
ስለተሰጠን እውቅና ከልብ እናመሰግናለን!
ግብር፣ ለሀገር ክብር!