ኢትዮ ቴሌኮም ሦስተኛውን እጅግ ፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ገንብቶ ሥራ አስጀመረ!

Bringing New Possibilities: Super-Fast Charging, Clean Energy! Go Green!

ኩባንያችን እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ መኪና ስነ-ምህዳር በስማርት ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየቱን አጠናክሮ በመቀጠል፣ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ፍየል ቤት አካባቢ የገነባውን ሦስተኛውን እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ በይፋ ወደ ሥራ አስገብቷል።

በሦስተኛ ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ሥራ የገባው ይህ ጣቢያ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ እና እጅግ የላቀ ቴክኖሎጂን (Advanced Technology) የሚጠቀም ሲሆን በተለይም የአውሮፓ ስሪት ለሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (European EV Cars) ጭምር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ያለውና ከተሽከርካሪዎቹ ዓይነት ጋር ራሱን የሚያጣጥም እጅግ ፈጣን (Super-Fast) ቻርጀር የተገጠመለት ነው።

ይህ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ ጣቢያ በአንድ ጊዜ እስከ 16 ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው በመሆኑ ለአሽከርካሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ የዚህ ጣቢያ ወደ ሥራ መግባትም፤ ኩባንያችን ቀደም ሲል የገነባቸውን ሁለት ጣቢያዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ 48 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን አቅም የፈጠረ ነው፡፡

የእስካሁኑ የጣቢያዎች አፈጻጸም እና አስተዋጽኦ

ኩባንያችን ከዚህ ቀደም ከቦሌ ወደ መገናኛ እንዲሁም ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስዱት ሁለት አቅጣጫ አውራ ጎዳናዎች ላይ፤ በአንድ ጊዜ 32 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸውን የኃይል መሙያ ጣቢያዎች ገንብቶ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡

እነዚህ ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት ከጀመሩበት ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ፣ ከ165 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን፣ ለዚህም 4,349,761.54 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም 6,081,447.62 ኪሎግራም ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ መከላከል የተቻለ ሲሆን፣ ይህም አበርክቶ ከ30,444 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር ይነፃፀራል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ስማርት ቴክኖሎጂ

በጣቢያዎቹ የተገጠሙት 16 እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኃይል መሙያዎች፤ እያንዳንዳቸው እስከ 180 ኪሎዋት በሰዓት የሚደርስ የመሙላት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ተሽከርካሪዎችን በከፍተኛ ፍጥነት ቻርጅ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በዘርፉ የመጨረሻው የልህቀት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ባህሪያት አሉት፡-

  • ስማርት አገልግሎት፡ሲስተሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመታገዝ፤ የተሽከርካሪዎችን የባትሪ ዓይነት እና የደንበኛውን ትዕዛዝ አስቀድሞ በመተንተን (Charging after diagnosing/analyzing) ራሱን በማስተካከል አገልግሎት ይሰጣል፡፡
  • የባትሪ ደህንነት፡ምንም ዓይነት የኃይል ብክነት የሌለው (Zero energy loss)፣ ከፍተኛ ብቃት ያለው እና ከስህተት የጸዳ (Zero error) ሲሆን፤ ባትሪን የመንከባከብ (Battery maintaining/restoring) አቅም አለው፡፡
  • በቀላሉ የሚዘምን (Scalability):ጣቢያዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በፍጥነት አቅማቸውን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የተገነቡ በመሆናቸው፣ እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም ጊዜ ማስፋፊያ ወይም ማሻሻያ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ወጥና ተጣጥሞ የሚሄድ የዲጂታል ቻርጂንግ ተሞክሮ በቴሌብር

  • የቻርጅማድረጊያጣቢያው 24/7 አገልግሎትየሚሰጥሲሆን፣ሙሉበሙሉየሚሰራውበቴሌብርሱፐርአፕላይበሚገኝመተግበሪያነው፡፡
  • የአገልግሎትክፍያተገልጋዮችፈጣን፣ቀላል፣ምቹናአስተማማኝበሆነውቴሌብርመፈጸምይችላሉ፡፡
  • ያለማንምአጋዥነት (Self-service) አሽከርካሪዎችአገልግሎቱንበራሳቸውማግኘትእናክፍያቸውንምበቴሌብርሱፐርአፕመፈጸምይችላሉ።
  • የስማርትኦንላይንክትትልስርዓቱበቴሌብርሱፐርአፕአማካኝነትመረጃዎችንለማግኘትእናየመሙላትሂደቱንለማስተዳደርየሚያስችልሲሆን፣ሲስተሙከክላውድሰርቨሮችጋርበፋይበርኬብልእንዲሁምበ4ጂእና 5ጂኔትወርክየተገናኘበመሆኑእጅግአስተማማኝነው፡፡
  • ኤን. ኤፍ. ሲ (Near Field Communication – NFC) በእጅበመንካትቻርጅማድረግ (tap to charge) ወይምስማርትየማንነትማረጋገጫ (smart authentication) ያላቸውሲሆን፣ይህምበቀላሉቻርጅማድረግንለማስጀመርእናክፍያዎችንእንዲያጠናቅቁበማስቻልተጠቃሚዎችየላቀተሞክሮእንዲኖራቸውያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያን ዲጂታል እና አረንጓዴ ትራንስፎርሜሽን ማጠናከር

ሀገራችን ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የትራንስፖርት ሥርዓት (Green Mobility) እያደረገች ያለውን ሽግግር ለመደገፍ፤ ኩባንያችን አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ዘመን ተሻጋሪ (Future-ready) መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ረገድ ፈርቀዳጅ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው ይህ ሦስተኛው እጅግ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ ጣቢያም፤ ኩባንያችን በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል መፍትሔዎች የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ገጽታ ለመለወጥ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives