ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር ፍሬያማ ስትራቴጂያዊ ውይይት

ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር ፍሬያማ ስትራቴጂያዊ ውይይት

ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር ፍሬያማ ስትራቴጂያዊ ውይይት አካሄደ

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳማይላ ዙባይሩ ጋር የተቋማችንን “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የግዙፍ የፋይናንስ አጋርነት ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም የተገበራቸው ስትራቴጂዎች የተቋሙን ጠንካራ የመፈጸም አቅምና አይበገሬነት በተግባር ያረጋገጡ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ ስኬት የተጫወተው ሚና የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፤ አዲሱ የ2028 ስትራቴጂም ከሀገራዊው የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣጣመ መሆኑን ገልጸዋል።ኢትዮ ቴሌኮም ከአገር ውስጥ ገበያ ባለፈ አገልግሎቶቹን በቀጠናው በማስፋፋት ለአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የማበርከት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት እንዳለውም አብራርተዋል።

ይህንን ግዙፍ ራዕይ ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም አፍሪካ አሁን ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘመን ዕድሎች በአግባቡ ለመጠቀም፤ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የቴሌኮም እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታን እንደ ቀዳሚ ተግባር መያዝ እንዳለባት አስገንዝበዋል።

የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳማይላ ዙባይሩ በበኩላቸው፤ ኢትዮ ቴሌኮም እያስመዘገበ ያለው አስደናቂ የዕድገት ጉዞ፣ የተቋሙ ጥንካሬና ባለራዕይ አመራር የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ ተቋሙ በጀመረው ቀጣይ የዕድገት ምዕራፍ ላይ በአጋርነት ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ኤ.ኤፍ.ሲ በመላው አፍሪካ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለሚያመጡ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

አቶ ሳማይላ ዙባይሩ አክለውም፤ “ይህንን የለውጥ ጉዞ በጋራ እናፋጥነው” በሚል ኢትዮ ቴሌኮም በመላው አፍሪካ የዲጂታል ተደራሽነትን፣ ፈጠራንና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስፋፋት ለያዘው ተልዕኮ ኮርፖሬሽኑ ንቁ ስልታዊ አጋር ሆኖ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል።

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives