ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር (Beyond Connectivity) መሪ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢ በመሆን የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለማዘመን እና ለማሳለጥ እንዲሁም የደንበኞቹን የዲጂታል እና ዘመኑን የዋጀ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከሰምሰንግ ኩባንያ ጋር በአጋርነት ለደንበኞቻችን የተለያዩ የሰምሰንግ ጋላክሲ የሞባይል ቀፎዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት በዛሬ ዕለት ፈጽሟል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የዋና ዋና ደንበኞቹን ፍላጎት ለመሟላት እና ለማሻሻል ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የስማርት ቀፎዎችን በተለያዩ የመክፈያ ዘዴዎች ሲያስገባና ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኩባንያው ከሰምሰንግ ኩባንያ ጋር በአጋርነት የሰምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የኢፒክ ጋላክሲ ኤስ23 አልትራ (epic Galaxy S23 Ultra)፣ ጋላክሲ ኤስ23 ፕላስ (Galaxy S23+) እና ጋላክሲ ኤስ23 (Galaxy S23) አቅርቦት በኢትዮጵያ ይፋ አደረጉ፡፡

ሁለቱ አጋር ኩባንያዎች ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ማንኛውም ሽያጭ ማዕከል አንድ ጋላክሲ ኤስ23 አልትራ (Galaxy S23 Ultra) ሲገዙ በብር 11,300 ዋጋ ያለው የጋላክሲ በድስ 2  (Galaxy Buds 2) በነጻ የሚሰጣቸው ሲሆን፣ እያንዳነዱን ጋላክሲ ኤስ23 ፕላስ (Galaxy S23+) እና ጋላክሲ ኤስ23 (Galaxy S23) ሲገዙ ደግሞ ብር 1,200 ዋጋ ያላቸውን ሲሊከን ሽፋን (silicone cover) በነጻ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

ጋላክሲ ኤስ23 (Galaxy S23 Ultra (12/512GB) በ140,000 ብር፣ ጋላክሲ ኤስ23 ፕላስ (Galaxy S23+ (8/256GB) በብር በ105,000 እና ጋላክሲ ኤስ23 (8/256ጂቢ) በብር 95,000 የሚሸጡ ሲሆን፣ በተጨማሪም እነዚህ የሞባይል ቀፎዎች/ዲቫይዞች የሃያ አራት ወራት ዋስትና ያላቸው ሲሆን ሰምሰንግ ኬር+ በሞባይል ቀፎዎቹ አገልግሎቶች ላይ ድንገተኛ ጉዳት እንዳይደርስ ጥበቃ መደረጉን ያረጋግጣል።

ሁለቱ አጋር ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገቡ የኢፒክ ጋላክሲ ኤስ23 (epic Galaxy S23) ዲቫይዞች ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የገበያ ድርሻን የማግኘትና የማስፋፋት ግብ ያለው ሲሆን፣ የኢፒክ ጋላክሲ ኤስ23 (epic Galaxy S23) ዲቫይዝ ካሜራ ተጠቃሚው በምሽት ጭምር ልክ ሲኒማ መሰል ቪዲዮዎችን እንደማንሳት የመሳሰሉ የፈጠራ ክህሎት እንዲኖረው የበለጠ ነጻነት የሚሰጠው ነው፡፡

የጋላክሲ ኤስ23 አልትራ (Galaxy S23 Ultra) ግራፊክስ አፈጻጻም (graphics performance) ከ40 ፐርሰንት በላይ ፍጥነት ያለው ሲሆን፣የአፈጻጸም አቅሙን ከ40 ፐርሰንት በላይ የፍጥነት መጠን በማሻሻል ወይም በማሳደግ (optimized) ለፎቶግራፊ፣ ለቪዲዮግራፊ እና እጅግ ፈጣን ለሆነ የጌም ዕይታ (low-latency gaming) እና ለመሳሰሉት አፈጻጸሙን እና የኃይል ፍጆታውን ማመጣጠን (balance performance) ያስችላል፡፡ የጋላክሲ ኤስ23 አልትራ (Galaxy S23 Ultra) የወደፊት የመጨረሻ/የላቀ የዲጂታል ዕድገትን ዕውን ማድረግ ታሳቢ ያደረገ እና የሞባይል ጌም ዕይታን በተመለከተ ቅጽበታዊ የጨረር ልየታን (real-time ray tracing) ለማድረግ የሚያግዝ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡

የጋላክሲ ኤስ23 አልትራ የእያንዳንዱን የብርሃን ጨረር በመለየት ተጠቃሚው ተንቀሳቃሽ ህይወት ያለው መሰል ዕይታዎችን ወይም ትዕይንቶችን ቀርጾ ለማየት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡   በተጨማሪ ጋላክሲ ኤስ23 የዲቫይዝ ዓይነቶች ሰምሰንግ ጋላክሲ ጥራታቸውን እና ውበታቸውን በጠበቀ ሁኔታ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ተጽዕኖ በማያስከትል ሁኔታ እንዲቀርብ የበለጠ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም

መጋቢት 5 ቀን 2015 .

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives