እንዲሁም የሁለት ተጨማሪ አሌክትሪክ መኪኖችን እና 5 ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጆችን የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር አከናወነ
ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃ ግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም በሁለተኛው ዙር ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ እና የአዳማ ባለ እድለኞች ሁለት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲሁም አራት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ቁልፍ በቃሉ መሠረት አስረክቧል፡፡
ኩባንያችን የ130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን በማስመልከት ባለፉት 35 ሳምንታት፣ 2 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለአዲስ አበባ እና ለወሊሶ ባለ እድለኞች እንዲሁም 4 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ለአርባምንጭ፣ሀረር፣ አርሲ ነጌሌ እና ለሆሳእና ባለእድለኛ ደንበኞቻችን ቁልፍ ማስረከቡ የሚታወስ ሲሆን፣ በተጨማሪም 201 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 16.8 ሚሊዮን ብር በቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ለ595 ደንበኞቻችን እንዲሁም ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ጥቅሎችን ጨምሮ እስካሁን ከ75.2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሽልማቶችን አበርክቷል።
በተጨማሪም በዛሬው እለት ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲሁም 5 ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን (ባጃጅ) እጣ የማውጣት መርሃ ግብር የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ አጋሮችና እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እና በቀጥታ ስርጭት በኩባንያችን ማህበራዊ ሚዲያ ሁሉም ድንበኞቻችን በተከታተሉት መርሃ ግብር እጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ በዚህም አሸናፊዎች የተለዩ በመሆኑ በቀጣይ በሚደረግ ዝግጅት ሁለቱን መኪኖች እንዲሁም አምስቱን ባጃጆች ለባለ እድለኞች የምናስረክብ ይሆናል፡፡
መርሃ ግብሩ በቀጣይ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፣ ደንበኞች አገልግሎቱን በመመዝገብ እየተጫወቱ ተጨማሪ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ቮልስዋገን አይዲ 4 (Volkswagen ID.4) እና ቢዋይዲ ዩዋን ፕላስ (BYD Yuan Plus SUV) መኪና ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ባለእድል የሚያደርጋቸዉ መሆኑ ተገልጿል።
ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም