ኢትዮ ቴሌኮም ዘመን ገበያ የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ በይፋ አስጀመረ!

በአፍሪካ የቴሌኮም እና የዲጂታል አገልግሎትን በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም  ላለፉት 130 ዓመታት በሀገራችን በሰፊው የቴሌኮም እና ዲጂታል አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ታላቅ ሀገርና ሕዝብ በማገልገል ላይ ይገኛል። ኩባንያችን ለሀገራችን ልማትና ኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና ያላቸውን ዘርፎች በመለየትና በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ በማስታጠቅ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያችን የዘረጋቸው የዲጂታል መሰረተ ልማቶች፣ ፈጣን ኢንተርኔት ግንኙነት፣ አስተማማኝ የክላውድ፣ ሞጁላር ዳታ ሴንተር እና የቴሌብር ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ወጣት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች መብዛት፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የሸማቾች ፍላጎት ማደግ፣ የስማርት ስልክ እና የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማደግ እንዲሁም መንግስት በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የኤሌክትሮኒክ ንግድን በተመለከተ ያስቀመጠው ስትራቴጂ ሀገራዊ የዲጂታል ግብይት  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ መደላድል ፈጥሯል፡፡

በመሆኑም ኩባንያችን ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት እውን እንዲሆን ባለው ቁርጠኝነት፣ ያለውን እምቅ የገበያ አቅም እንዲሁም መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም የዲጂታል ኢኮኖሚ ትሩፋትን በሙሉ አቅም ለመጠቀም አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተማከለ ዲጂታል ግብይት ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት የሀገራችንን የግብይት ሥርዓት በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል፣ አካታች፣ ምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎችን ከሸማቾች የሚያገናኝ ዘመን ገበያ የተሰኘ የዲጂታል ገበያ በይፋ ማስጀመሩን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ይህ የዲጂታል ገበያ ለሀገራችን አዲስ ምዕራፍ የምናበስርበት፣ ፈጠራ እና ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ለሁሉም ዜጎች ለማድረስ መሰረት የሚጥል ሲሆን በተለይም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሸማቾች ጋር በቀላሉ ለማገናኘት፣ ለማብቃት እና አዳዲስ የገበያ እድል በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚን ትሩፋት አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል ነው።

 ዘመን ገበያ ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ

  • ለኢኮኖሚ እድገት፦ዘመን ገበያ ንግድን በማቀላጠፍና ከአነስተኛ ንግድ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በማገናኘት፣ የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
  • ለሥራ ዕድል ፈጠራና የኢኮኖሚ እድገትበሎጂስቲክስ፣ በዲጂታል አገልግሎቶች፣ በዲጂታል ገበያ፣ በችርቻሮና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የአገር ውስጥ የሥራ ዕድሎችን በማነቃቃት ዘላቂ የኑሮ መተዳደሪያንና የማኅበረሰብ እድገትን ይደግፋል።
  • ለዲጂታል አካታችነት፦በከተማ፣ በከፊል ከተማና በገጠር ማህበረሰቦች ላሉ ተጠቃሚዎች ተደራሽ የሆነ አገልግሎት በማቅረብ የዲጂታል ክፍተትን በማስወገድ፣ የዲጂታል ክህሎትን እንዲሁም በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳትፎን ያሳድጋል።
  • ለአገር አቀፍ ተደራሽነት፣ አካታችና ሰፊ የገበያ ተደራሽነት፡- ዘመን ገበያ የከተማና የገጠር ማህበረሰቦችን በማገናኘት በመላው ሀገራችን በዲጂታል ንግድ ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖር ያስችላል።
  • ለቅልጥፍናና ምርታማነት፦የግብይት ሂደቶችን ማሳለጥ፣ ቀልጣፋ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ያስገኛል፣ የዋጋ ግኝትን ያፋጥናል እንዲሁም የገበያ ግልጽነትን ያሳድጋል፤ ይህም ለአምራቾችም ሆነ ለሸማቾች የላቀ ዋጋ ያስገኛል።
  • ለፋይናንስ አካታችነት፦የዲጂታል ክፍያዎችን በማበረታታት የፋይናንስ አካታችነት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ይህም ብዙ ሰዎች በመደበኛው ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል።
  • ለአገር ውስጥ ምርት፦የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች፣ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎችና አምራቾች ምርቶቻቸውን በመላ አገሪቱ አልፎ ተርፎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያሳዩና እንዲሸጡ የሚያስችል ጠንካራ ፕላትፎርም ያቀርባል።
  • ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) እድገትና የሥራ ፈጠራንማሳደግ፦
    ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲያድጉ፣ አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥሩና በሰፊው ፕላትፎርም እንዲወዳደሩ የሚያስችሉ መደላድሎችን ይፈጥራል።
  • በቂ መረጃ ለማግኘትመድረኩ ስለ ገበያ አዝማሚያዎች፣ የሸማቾች ባህሪና የአቅርቦት ሰንሰለት እንቅስቃሴዎች ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያመነጭ በመሆኑ ለፖሊሲና ለንግድ ውሳኔዎች ግብዓት ይሆናል።
  • የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንንማፋጠን፦ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ራዕይ የሚደግፍ ሲሆን ከዲጂታል ኢትዮጵያ ካሉ ብሔራዊ ስትራቴጂዎች ጋር ይጣጣማል።
  • የድንበር ተሻጋሪ የንግድ ዕድሎችንማመቻቸት፦ በቀጣይ የአገር ውስጥ አምራቾችና ነጋዴዎች ዓለም አቀፍ ገበያዎችን እንዲያገኙ በማስቻል ለወጪ ንግድ ዝግጁነትንና የኢኮኖሚ ብዝኃነትን ያሳድጋል።
  • ለዓለም አቀፍ ገበያ ዝግጁነት፦ የአገር ውስጥ አምራቾች ከአገር ውስጥ ገበያዎች ባለፈ በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ መሣሪያዎችን፣ ፕላትፎርም እና ተሞክሮ ያሟላላቸዋል።
  • ለዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት፦ ባህላዊ የገበያ ስልቶችን በማዘመንና የአገር ውስጥ ኢኮኖሚን በማጎልበት ለኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
  • አንድ የተቀናጀ የዲጂታል ገበያ፦ በከተማና በገጠር ያለውን የግብይት ልዩነት በማስወገድ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚደግፍ አንድ ወጥ ዲጂታል ገበያ ይፈጥራል።

ለምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎች

ዘመን ገበያ ለነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ዕደ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና ለንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች ያስገኛል፦

  • ሰፊ የገበያ ተደራሽነት፦የተለምዶ መደብሮችን የጂኦግራፊያዊ ገደቦች በማለፍ አገር አቀፍ የደንበኛ መሠረት ለማግኘት፤
  • የሥራ ማስኬጃ ወጪ ለመቀነስ፦ከአካላዊ የችርቻሮ ቦታዎች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ወጪ መኖሩ፤
  • የደንበኛ ግንኙነት ለማሳደግ፦ከደንበኞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለመገንባት፣ ግብረመልስ ለመሰብሰብና የምርት ብራንድ ታማኝነትን ለመገንባት፤
  • ለዕቃ ክምችት አስተዳደር፦የዕቃ ክምችትን በቀላሉ ለማስተዳደር፣ ሽያጭን ለመከታተልና የፍላጎት ትንበያ ለመስጠት፤
  • ለዲጂታል ክፍያ መፍትሔዎችን፦ደህንነታቸው የተጠበቁና ምቹ የክፍያ መቀበያ መንገዶችን ያስገኛል፤
  • ለገበያና ማስታወቂያ፦ምርቶችን ለማስተዋወቅና ለታለመላቸው ታዳሚዎች ለማድረስ የሚያስችሉ ገጽታዎች እንዲሁም ቀላል የመረጃ ትንተና (Data Analysis) እና አዳዲስ የሽያጭ እድሎች የሚሉት ናቸው፡፡

ለሸማቾች ያለው ፋይዳ

በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አምጪ የዲጂታል ገበያ ለመሆን በማለም ለሀገሪቱና በኢኮኖሚዋ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ተዋናዮች በማገናኘት ጉልህ ፋይዳ የሚያበረክት ሲሆን በከተሞችና በገጠር ያሉ ሸማቾች ሰፊ የምርት እና አገልግሎት አማራጭ እንዲኖራቸው፣ ምቹና ተደራሽ አገልግሎት ለማግኘት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ የዲጂታል ክፍያ አማራጭ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

ለሎጂስቲክስ ኩባንያዎች

ሰፊና ተደራሽ ገበያ ለማግኘት፣ በመረጡ የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ለማተኮር፣ በመረጃ ላይ የተደገፉ የአገልግሎት ማሻሻያዎች ማድረግ፣ የአገልግሎት አፈጻጸምንና የደንበኛ ግብረመልስን በመከታተል የአገልግሎት ማሻሻያዎች ለማድረግ፣ የተማከለ የሥራ እድሎች ለማግኘት እንዲሁም በዲጂታል ሥነ-ምህዳር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ተዋናዮች በማገናኘት ፈጠራንና ትብብርን ለማሳደግ ያስችላቸዋል።

የዘመን ገበያ ዋና ዋና ገጽታዎች

ዘመን ገበያ ለደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒአፕ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን፣ የነጋዴዎች ፖርታል እና ሞባይል መተግበሪያ፣ የሸማቾች ሞባይል መተግበሪያ፣ የሎጂስቲክስ አስተዳደር ሥርዓት፣ የላኪዎች (Dispatcher) ሞባይል መተግበሪያ እና የሲስተም አድሚንስትሬሽን ፖርታል አሉት።

የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ በጋራ እንገንባ!

ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት ለመስራት ያቀረብነውን ጥሪ ተከትሎ ከ42 በላይ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ ኩባንያችን በቀጣይም ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት በመስራት የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት በማራመድ ጉዞ ውስጥ የበኩላቸውን ለማበርከት ለሚፈልጉ በመላ ሀገራችን ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች እና የሎጂስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች ጥሪውን ያቀርባል።

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ፡ የተለያዩ የኔትዎርክ እና የፖወር ዕቃዎችን፣ የእንጨት ፖሎችን እና ኮምቦልቻ የሚገኘውን የፖል መቀቀያ ማሽን፣አዳዲስ ኘሪንተሮችን፣ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ እና ኤል.ኢ.ዲ መብራቶች እና የእሳት ማጥፍያዎችን፣ ቁርጥራጭ የኤች.ዲ.ፒ ዳክቶች፣ ብረታ ብረቶች፣ ካርቶኖች እና ወረቀቶችን፣ የእንጨት ማሸጊያ ሳጥኖች፣ አጣናዎች እና ፓሌቶችን ባሉበትሁኔታበጨረታአወዳድሮመሸጥይፈልጋል፡፡

Read More »
Archives