Partnership For Global Reach!

Ethio telecom collaboration with stc

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳውዲ ቴሌኮም የቢዝነስ አጋርነታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ!

በሳውዲ ቴሌኮም የሴልስ ከርየር እና ሆልሴል ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዚያድ ሃማድ ኤ. አልሃሶን እና የከርየር ሴልስ ዳይሬክተር ሚስተር ባንደር ኤ. አልኮዳይር የተመራ ልዑክ ከኩባንያችን ማኔጅመንት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ ውይይቱ በሁለቱ ኦፕሬተሮች መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን፣ በተለይም ነባሩን የቢዝነስ ትብብር ለማሳደግ፣ አዳዲስ የዕድገት አማራጮችን ለመክፈት እና የተለያዩ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

ውይይቱ በዋና ስራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ሲሆን፣ ዋና ስራ አስፈፃሚያችንም “ለጋራ ተጠቃሚነት ብዙ ልንተባበርባቸው እና አዳዲስ የዕድገት አማራጮችን ልንፈልግላቸው የምንችላቸው ዘርፎች አሉ ያሉ ሲሆን፤ እነዚህም የአገሮቻችንን ዲጂታል ሽግግር የሚያሳድጉ እና ይበልጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን የሚያፋጥኑ ዕድሎች ናቸው” ብለዋል።

ውይይቶቹ የዲጂታል መሠረተ ልማት አቅሞችን ለማስፋፋት፣ የሆልሴል ቢዝነስ ትብብርን እና የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች ውህደትን ለማጠናከር ተጨባጭ ስትራቴጂዎችን ለመዳሰስ ያስቻለ ሲሆን፣ በተለይም ሁለቱም ኩባንያዎች የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማሳደግ፣ የድንበር ተሻጋሪ የሀዋላ እና የክፍያ ሥነ ምህዳሮችን ለማጠናከር እንዲሁም ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት ለማቅረብ ቴሌብር እና ሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የክፍያ ሲስተሞችን ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል።

የሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ ልዑካን የኢትዮ ቴሌኮምን የላቀ የቢዝነስ አፈፃፀም ብቃት አስመልክቶ ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ሲሆን፣ በተለይም ባለፉት ስድስት ዓመታት ኩባንያው ያስመዘገባቸው አስደናቂ ለውጦች እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በመምራት ለተገኘው ስኬትም ከፍተኛ እውቅና ሰጥተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ ያላቸውን ሀብት እና የጋራ ትብብር ሆልሴልን እና ከርየርን ለማስፋፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን፣ በተለይም በፊንቴክ፣ በአለም አቀፍ ሀዋላ፣ በተለያዩ የዲጂታል መፍትሄዎች እና በርካታ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ አዳዲስ እድሎችን በር የሚከፍት ይሆናል፡፡ ይህ አጋርነት ወደ አንድ ትንሽ መንደርነት በመቀየር ላይ ባለበት ዓለም ውስጥ የዲጂታል ተደራሽነትን፣ ፈጠራን እና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማሳደግ ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives