በወቢ የክሬዲት አገልግሎት በ45 ቀናት ውስጥ የሚመለስ ከ100 ብር ጀምሮ እስከ 30,000 ብር ድረስ አነስተኛ ብድር ማግኘት ያስችላል።
ወቢ ብድር
| የብድር መጠን | የብድር ገደብ(ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ) | የአገልግሎት ክፍያ | ዕለታዊ ክፍያ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|
| የ5 ቀን ወቢ | ክ100 – 5,000 ብር | 1.50% | 0.70% | 0.11% |
| የ10 ቀን ወቢ | ክ100 – 6,000 ብር | 2% | 0.55% | 0.11% |
| የ30 ቀን ወቢ | ክ100 – 15,000 ብር | 4% | 0.70% | 0.11% |
| የ45 ቀን ወቢ | ክ100 – 30,000 ብር | 6.50% | 0.55% | 0.11% |
የወቢ ደሞዝ ክሬዲት እዚህ ያንብቡ
ወቢ ደሞዝ ክሬዲት
ወርኃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር ወይም በስንቄ ባንክ በኩል ለሚከፈላቸው የመንግሥትና ግል ተቋማት ሠራተኞች፤ የአምስት ወር ደመወዝ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ ብድር ማስገኝት የሚያስችል የክሬዲት አገልግሎት ነው። ይህ የብድር አቅርቦት በ14 ወራት ውስጥ የሚከፈል ሲሆን፤ በዓመት እስከ 1.3 ቢሊየን ብር የሚደርስ የብድር ክፍያ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
| መጠን | የብድር አይነት | የአገልግሎት ክፍያ | ክፍያ በወር | የክፍያ ጊዜ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|---|
| 1,000 – 1,000,000 Birr | 5 Months | 19.50% | 1.39% | 14 Months | 0.11% |
ወቢ(አነስተኛ ብድር) አገልግሎትን ለማስጀመር እና ለመጠቀም
ደንቦች እና ሁኔታዎች
ዉል
I.ይህ ዉል (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች") እየተባለ የሚጠራው) የቴሌብር ወቢ የብድር አገልግሎት ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
II.እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የቴሌብር ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት በደንበኛዉ ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ ("ለማስጀመር" የሚለውን ምርጫ ሲጫን) በደንበኛው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- ትርጓሜ
በዚህ ደንቦች እና ሁኔታዎች ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት የሚከተለውን ትርጉም ይይዛሉ፡-
- "ሲንቄባንክ" ማለት ቁጥጥር የሚደረግበት የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለቴሌብር ደንበኞች ወቢ አነስተኛ የክሬዲት አገልግሎት ለመስጠት የተስማማ የፋይናንስ ተቋም ነው።
- "ኢትዮ ቴሌኮም" ማለት የክፍያ መፈጸምያ ሰነድ አዉጭነት ፍቃድ ያለው እና በሲንቄ ባንክ ለሚሰጠዉ ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት የማመቻቸት ሥራ ለመስራት ስምምነት ያለው ተቋም ነው፡፡
- "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ" ማለት በአዋጅ ቁጥር. 718/2003 (1282/2015 እንደተሻሻለዉ) መሠረት ለፋይናንስ ተቋማት ፍቃድ ለመሰጠትና ሥራቸዉን ለመቆጣጠር ሥልጣን ያለዉ ተቋም ነው።
- "ቴሌብር” ማለት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸዉን በመጠቀም የፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም ነው፡፡
- "የቴሌብር አካውንት" ማለት የቴሌብር ተጠቃሚ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ገንዘብ የሚያስቀምጡበት፣ የሚላላኩበት እና የሚቀበሉበት አካዉንት ነዉ፡፡
- "ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት" ማለት በሲንቄ ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም የጋራ ትብብር ግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ብድር በቴሌብር አማካኝነት የሚያገኙበት የአገልግሎት ዓይነት ነው።
- "ወቢየደመወዝ የብድር አገልግሎት" ማለት ለግል እና ለመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ከየተቋማቸዉ ጋር በሚደረግ ስምምነት በዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በቴሌብር አማካኝነት ሲንቄ ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ የብድር አገልግሎት ነው
- “ግለሰብደንበኛ” ማለት የተፈጥሮ ሰዉ ሆኖ በስሙ የቴሌብር አካውንት ያለዉና ቴሌብር ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለመዉሰድ የተስማማ ሰዉ ማለት ነው።
- ”ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ /ኢ- መኒ” ከ ኢትዮጵያ ብር ጋር እኩልመጠን ያለው ገንዘብን የሚወክል ፣ ግለሰብ ደንበኛው የሚያስተዳድረዉ እና በደንበኛዉ የቴሌብር ሂሳብ ዉስጥ የሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
- "አንተ" ወይም "የአንተ" ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን የግለሰቡን የግል ተወካዮችም ያጠቃልላል።
- “እኛ" "አኛን" እና "የእኛ” ማለት ሲንቄ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት ነው፡፡
- “የአገልግሎት ክፍያ ” ማለት ለወቢ አነስተኛ ብድር አገልግሎት በመጀመሪያዉ ቀን በግለሰብ ደንበኞች የሚፈፀም ክፍያ ነው ::
- ”ዕለታዊ ክፍያ ” ማለት ሳይከፈል በቀረዉ የዕዳ መጠን ላይ ግለሰብ ደንበኛዉ በወሰደዉ የብድር ዓየነት መሠረት በየዕለቱ የሚፈፀም የክፍያ ዓይነት ነዉ ፡፡
- "የቅጣት ክፍያ" ማለት ግለሰብ ደንበኛዉ በገባዉ ዉል መሠረት የብድሩን ገንዘብ ሳይከፍል የቀረ እንደሆን የሚከፍለዉ ገንዘብ ነዉ፡፡
- "የክፍያ ቀን " ማለት ግለሰብ ደንበኛዉ የወሰደዉን ብድር ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ የሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ቀን ነወ ፡፡
- "የተበላሸ ብድር" ግለሰብ ደንበኛዉ ብድሩን አጠናቆ እንዲከፍል ከሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ዕለት ጀምሮ ከሚቆጠር 90 ቀናት በኋላ ያልተከፈለ ብድር ማለት ነዉ
- በአነስታይ ፆታ የተገለፁ ለተባዕታይ ፆታ እንደዚሁም በተባዕታይ ፆታም የተገለፁ ለአነስታይ ፆታ ያገለግላሉ፡፡
- ግለሰብ የሚለዉ ቃል ወንድና ሴት ፆታን ለመግለፅ ያገለግላል ፡፡
- ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
- ይህአነስተኛ የብድር አገልግሎት ሲንቄ ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ ሲሆን ለብድሩ የዋለዉ ገንዘብ በስንቄ ባንክ የቀረበ ነዉ ፡፡
- ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎትን ለማስጀመር ግለሰብ ደንበኛዉ USSD (*127#) ወይም የቴሌብርን መተግበሪያ መጠቀም ይችላል፡፡
- ወቢየብድር አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት ይህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ እና በመረዳት መስማማት ይኖርብዎታል፡፡
- በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር ምርጫዉ ዉስጥ “ለማስጀመር” የሚለውን ምርጫ አይጫኑ፡፡
- “ለማስጀመር” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋጋጡ ወይም ብድር ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
- ወቢአነሰተኛ የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ብቻ በቴሌብር ለመጠቀም ተስማምተዋል።
- ደንብእና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም በስንቄ ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን ይህንንም ለዉጥ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አስቀድሞ እንዲደርስዎት ይደረጋል። እነዚህ ለዉጦች በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በኢትዮቴሌኮም ድረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
- ደንብና ሁኔታዎች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ተቀባይነት ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ በእርስዎ እና በእኛ መካከል በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ውል ይሆናሉ። በዚህ ስምምነት ስር ያለዎትን ማንኛውንም መብት ወይም ግዴታ ለሌላ ለማንም ማስተላለፍ አይፈቀድልዎትም።
- ግለሰብ ደንበኛውገንዘቡን ለህጋዊ ዓላማ ብቻ ለማዋል ተስማምቷል።
- የወቢ ብድር አገልግሎትን ለማስጀመር
የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-
- እነዚህንደንቦችና ሁኔታዎችን ሊያነቡ፣ሊረዱ እና ሊስማሙ ይገባል፣
- 18ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን፣
- አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ፣
- የቴሌብርእና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ መሆን አለብዎት፡፡
- የቴሌብርየደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት፡፡
- ወቢ አነሰተኛ ብድር ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች፤
- የግለሰብ ደንበኛው የመበደር አቅም፣ ደንበኛው የብድር ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ፣ቀደም ሲል የወሰደዉን ብድር የመክፈል ታሪክእና በቴሌኮም አገልግሎት አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች የደንበኛ የብድር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
- የአየርሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)፣
- ዕቃወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም፣
- ቢልክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
- ለእርስዎወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
- በልክ ዲስፐርስመንት ( የቀን ሠራተኞች ክፍያ ፣ደመወዝ ፣ዕርዳታ፣ጡረታ፣…) ክፍያ በቴሌብር መቀበል፣
- ከውጭአገር ገንዘብ መቀበል፣
- የትኬት ግዢ፣
- ለገንዘብማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ( ፈንድ ረይዚንግ)፣
- በቴሌብር ወኪሎች በኩል ገንዘብ መቀበልና ወጪ ማድረግ፣
- የቁጠባአገልግሎት፣
- ገንዘብመላክ፣
- የቴሌኮምፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)፣
- በቴሌብር የተወሰደን ብድር በአግባቡ የመክፈል የቀደመ ታሪክ ፡፡
- ብቁለመሆን ደንበኞች ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም አለባቸው፡፡
- ወቢየደመወዝ የብድር አገልግሎት ለማግኘት ወርሃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል እና ከሚሰሩበት ተቋም ጋር የሚደረግ ስምምነት በቂ ነዉ፡፡
- የብድሩ መጠን እና ክፍያ
- የግቢይት መጠንዎን መሠረት በማድረግ በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ፡፡
- በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 576/2018 መሠረት ለኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ ከጠየቁት ጠቅላላ የብድር መጠን ላይ አንድ በመቶ (1%) ተቀናሽ ተደርጎ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ሌላ ብድር ለማግኘት መጀመሪያ ከቴሌብር የወሰዱትን ብድር መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
- ያለብዎትን ብድር በከፊል ወይም በሙሉ በአንድ ጊዜ መክፈል ይችላሉ
- የክሬዲት ክፍያ ቀን ብድሩን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እንደ ብድሩ ዓይነት 5 ቀን፣10 ቀን ፣ 30 እና 45 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
- ለ5 ቀናት ለ10 ቀናት ለ30 ቀናት እና ለ45 ቀናት ከፍተኛው የብድር መጠን እንደ ቅደም ተከተላቸው 5,000 ብር6,000 ብር 15,000 ብር እና 30,000 ብር ነው። ከላይ ለተጠቀሱት የክሬዲት ቀናት ዝቅተኛው የብድር መጠን በቅደም ተከተላቸው 100 ብር፣ 100 ብር 200 ብር እና 2,500 ብር ነው።
- ያለብዎትንየአምስት ቀን ክሬዲትዎን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከከፈሉ፤ በመጀመሪያዉ ቀን የአገልግሎት ክፍያ 5% የሚከፍሉ ሲሆን በቀሪዉ የመክፍያ ጊዜዎ የክሬዲት ገደብ ላይ በመመስረት ዕለታዊ ክፍያ ከ0.35% እስከ 1.2% ይከፍላሉ፡፡
- የአስርቀን ክሬዲትዎን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከከፈሉ፤ በመጀመሪያዉ ቀን የአገልግሎት ክፍያ 2% የሚከፍሉ ሲሆን በቀሪዉ የመክፍያ ጊዜዎ የክሬዲት ገደብ ላይ በመመስረት ዕለታዊ ክፍያ ከ 0.3% እስከ 9% ይከፍላሉ፡፡
- የሰላሳቀን ክሬዲትዎንበተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከከፈሉ፤ በመጀመሪያዉ ቀን የአገልግሎት ክፍያ 4% የሚከፍሉ በቀሪዉ የመክፍያ ጊዜዎ የክሬዲት ገደብ ላይ በመመስረት ዕለታዊ ክፍያ ከ0.3% እስከ 1% ይከፍላሉ
- የአርባ አምስት ቀን ክሬዲትዎንበ ተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከከፈሉ፤ በመጀመሪያዉ ቀን የአገልግሎት ክፍያ 5% የሚከፍሉ ሲሆን በቀሪዉ የመክፍያ ጊዜዎ የክሬዲት ገደብ ላይ በመመስረት ዕለታዊ ክፍያ ከ0.5% እስከ 0.67% ይከፍላሉ፡፡
- ለወቢ ደመወዝ የብድር ክፍያዉ በወሰዱት የብድር ጊዜ ተከፋፍሎ ቀስ በቀስ ይከፈላሉ
- የ5 ወር የወቢ ደመወዝ ክሬዲት የ 14 ወራት የመክፈያ ጊዜ እና 5% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
- የ3ወር የወቢ ደመወዝ ክሬዲት የ 9 ወራት የመክፈያ ጊዜ እና 14% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
- የ1ወር የወቢ ደመወዝ ክሬዲት የ 3 ወራት የመክፈያ ጊዜ እና 12% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
- ያለብዎትን ብድር በክፍያ ቀን ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ 0.11% በየዕለቱ ይከፍላሉ፡፡
- በጉርሻየሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
- ያልተፈፀመ ክፍያ አሰባሰብ
- የሚጠበቅብዎትን ክሬዲት ክፍያ በሰዓቱ ካልፈፀሙ ኢትዮ ቴሌኮምእና /ወይም ሲንቄ ባንክ የቀረውን የብድር መጠን ከቴሌብር ሂሳብዎ ወይም ከቁጠባ አካውንቶ ወዲያውኑ ተቀናሽ ያደርጋሉ፡፡
- ብድሩ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ሲንቄ ባንክ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከባለዕዳዉ ሲንቄ ባንክ ወይም ሌሎች ባንኮች ሒሳብ በቀጥታ መቁረጥን ጨምሮ ማናቸዉም አማራጭ ዜዴዎች በመጠቀም ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
- ከፍርድቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን ለመሰብሰብ ያግዝ ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ሲንቄ ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን የመኖሪያ ወይም የሥራ አድራሻ ማናቸዉም አማራጭ ዘዴዎች በመጠቀም አፈላልገዉ በማግኘት ዕዳዉን የመሰብሰብ መብት ያላቸዉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
- ዕዳዉመከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሸን ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን አድራሻ እና ሌሎች ለእዳው አሰባሰብ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመሰብሰብ ሥራ ላይ ለሚሳተፍ ሦስተኛ ወገን (ድርጅት ወይም ግለሰብ) አሳልፈዉ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
- ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉ የማይከፈል ከሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሽን ባንክ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በራሳቸዉ ወይም በሌላ የሕግ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም በግለሰብ ጠበቃ አማካኝነት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አላቸው፡፡
- ተፈጻሚነትያለው ህግ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የሲንቄ ባንክና የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው የአሠራር ሥርዓቶች በእነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መረጃስለመጠየቅ
ስለ ወቢ አገልግሎት፣ ሂደት፣ ደንብ እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል), ወደ 126 አጭር ጽሁፍ መልዕክት በመላክ፣ በሶሻል ሚዲያ (https://telehub.ethiotelecom.et/) ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- የውልመቋረጥ
ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱንም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።
- ቅሬታእና የግጭት አፈታት
ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልረኩ ጉዳዩን ወደ ሲንቄ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅሬታዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር ሰላሳ ቀናት ዉስጥ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ጉዳዮቻቸውን በኢትዮጵያ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ብቻ ለማቅረብ ተስማምተዋል።
- የመያዝመብት
እዳዎን ካልከፈሉ በተለይም በጥሬ ገንዘብ፣ዕቃዎች፣ዋስትናዎች፣ውድ ጌጦች፣ቼኮች እና ማንኛውን ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይነቀሳቀስ ንብረትዎ ላይ አጠቃላይ የመያዝ መብት ይኖረናል፡፡እኛ ጋር ያለቦትን እዳ መክፈል የማይችሉ ከሆነ እና የማቻቻል መብት ሲፈጠር በመያዣ መብት ስር የተያዙ ንብረቶችን ላልተከፈለው ብድር እንደ ዋስትና ተደርጎ መቁጠር ይቻላል፡፡
- ዕዳስለማቻቻል
የወሰዱትን አነስተኛ ብድር መጠን እንዲከፍሉ ካሳወቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ ቁጠባ፣ተርም ዲፖዚት፣የጋራ ወይም የተናጠል ከሆኑት ላይ ያለብዎትን ዕዳ መጠን ያህል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መዉሰድ እንድንችል ተስማምተዋል፡፡
- ማስተባበል
የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት ከእርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። የሚስጥር ቁጥርዎን ሌላ ሶስተኛ ወገን እንዲያዉቀዉ በማድረግዎ ወይም በየጊዜው ባለመቀየርዎ፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አጠቃቀም በማከናወንዎ፣ የሞባይል ስልክዎ ወይም ሲም ካርድ ሲሰረቅብዎ ወይም ሲጠፋብዎ ለሚመለከተዉ አካል ፈጥነዉ ባለማሳቅዎ እና ባለማስዘጋትዎ የሚደርስብዎ ኪሳራ /ጉዳት የእርስዎ ኃላፊነት ብቻ ይሆናል፡፡