ከሚጠቀሙት የቴሌኮም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ድጋፍ ሲፈልጉ ፈጣንና ምቹ የራስ አገዝ አገልግሎት ወደ 994 መልዕክት በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከዚህ በፊት በ8994 ሲያገኙ የነበረዉን በራስ አገዝ ለማይመለሱ ጥያቄዎች የቀጥታ መስመር ሰራተኞችን ድጋፍ ለማግኘት ወደ 994 መልዕክት ከላኩ በኃላ ከ994 በሚደርሰዎ ማውጫ መሰረት ከታች ያለዉን ቅደም ተከተል ይከተሉ፡-
ለምሳሌ፡-
ብልሽት ማስመዝገብና ያስመዘገቡትን ብልሽት የጥገና ሂደት በ994 ራስ አገዝ አገልግሎት ለመከታተል
1.ማንኛዉንም ፊደል ወደ 994 መላክ
2.በመቀጠል ወደ 994 በቁጥር 01 ብሎ መላክ
3.0* ከሚልኩት መልእክት በማስቀደም የተበላሸዉን አገልግሎት ቁጥርና ሰልክ ቁጥራዎን መላክ
4.ከ994 መልስ እስከሚደርስዎ ይጠብቁ
ማስታዎሻ፡-
የቀጥታ መስመር ሰራተኞችን የሚያገኙበትን አማራጭ ከመጠቀምዎ በፊት በራስ አገዝ አገልግሎት ለመገልገል መሞከር አለብዎት፡፡
ሁሌም ወደ ቀጥታ የመስመር ላይ መስተንግዶ ሰራተኞች መልዕክት ሲልኩ 0* ማስቀደም ይኖርብዎታል፡፡


