ዲጂታል አፍሪካን እውን እናደርጋለን

Ethio telecom signs MOU with FEWA, Welcomes Rwandan Education Minister  Ethio telecom proudly hosted a distinguished delegation, led by Hon. Joseph Nsengimana, Rwanda's Minister of Education, and joined by our esteemed partners, FEWA (Future of Education & Work in Africa), at our MWC Kigali 2025 exhibit on October 23rd.  Our leadership showcased our innovative smart education solution, garnering significant interest from Hon. Nsengimana, who expressed a strong desire for Africa to adopt this advanced digital solution framework.  Following this, Ethio telecom and FEWA signed a pivotal Memorandum of Understanding (MoU). This MoU reinforces our shared determination to collaboratively realize smart education and catalyze meaningful transformation across the sector in Rwanda and throughout Africa.  This strategic partnership is a concrete step in advancing our "Next Horizon: Digital & Beyond 2028" strategy. It positions both of us to establish regional collaborations in digital solutions, thereby fostering inclusion and innovation to forge an inclusive, AI-ready future for Africa.  Ethio telecom

ኩባንያችን በሩዋንዳ ስማርት ትምህርት ሶሉሽን ለመተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

ኢትዮ ቴሌኮም በሩዋንዳ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 2025 ኪጋሊ የሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ (MWC) ላይ በክቡር ዶ/ር ጆሴፍ ንሴንጊማና የሩዋንዳ የትምህርት ሚኒስትር የተመራውን ልዑካን ቡድን እና ከFEWA (Future of Education & Work in Africa) የተወከሉትን ልዑካን አጋሮቻችን እ.አ.አ. ኦክቶበር 23 ቀን 2025 በኪጋሊ አውደርዕያችን ላይ ጉብኝት በማድረጋቸው ታላቅ ኩራት ይሰማናል፡፡

የኩባንያችን አመራሮች ፈጠራ ላይ የተመሰረቱ አዳዲስ የስማርት የትምህርት ሶሉሽኖችንን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ በዚህም ክቡር ዶ/ር ንሴንጊማና የተሰማቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚንስትሩም አፍሪካ ይህንን የላቀ ዲጂታል ሶሉሽን ማዕቀፍ በመጠቀም የትሩፋቱ ተቋዳሽ መሆን አለባት ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ኩባንያችን እና FEWA ወሳኝ የሆነ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) የተፈራረሙ ሲሆን፣ ይህ የመግባቢያ ስምምነት በሩዋንዳ እና በመላው አፍሪካ ስማርት ትምህርትን በጋራ ለማሳካት እና በትብብር በዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ይሆናል።

ይህ ስትራቴጂያዊ አጋርነት “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ”ን ወደፊት ለማራመድ የተወሰደ ተጨባጭ እርምጃ ሲሆን፣ ይህም ኩባንያችን እና FEWA በጋራ በዲጂታል ሶሉሽኖች ረገድ ቀጠናዊ ትብብር ለመመስረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ይህም  ሁሉን አቀፍ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዝግጁ የሆነች፣ የዲጂታል አካታችነትን እና የፈጠራ ዕድገትን ያጠናከረች አፍሪካን እውን ለማድረግ የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives