በቫውቸር ካርድ እና ይሙሉ የአየር ሰዓት የማከፋፈል ስራ መስራት ለምትፈልጉ

በቫውቸር ካርድ እና ይሙሉ የአየር ሰዓት የማከፋፈል ስራ መስራት ለምትፈልጉ ከታች ባለው መስፈርት መሰረት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብርት እንገልጻለን፡

መስፈርት:-

 1. ከዚህ በፊት በጥቁር መዝገብ ዝርዝር/blacklist/ ውስጥ ያልገባ፤
 2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና በአዲስ አበባ ክልል ብቻ መስራት የሚችል፤
 3. በንግድ ፈቃዱ ላይ ብር200,000.00 እና ከዛ በላይ ካፒታል ያለው፤
 4. የቫውችር ካርድና ይሙሉ አየር ሰዓት ግዥ ሁኔታ
 • ውል ከተፈረመ በኋላ ቢያንስ የ 2 ሚሊዮን ብር ባንክ ዋስትና (unconditional bank guaranty) በማቅረብ ለአንድ ወር በሚቆይ የዱቤ ሽያጭ ወይም ቢያንስ የ2ሚሊዮን ብር ሲፒዮ (CPO) በማቅረብ በካሽ በመግዛት፡፡
 1. ውርሃዊ እቅድ/target/
 • ኢትዮ ቴሌኮም በየጊዜው የሚሰጠውን የግዥ እቅድ እንደሁኔታው የመቀየር ስልጣን አለው፤
 • አዲስ አከፋፋዮች ያለ ግዥ እቅድ የሚሰሩበት የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ አላቸው፡፡
 1. ኮሚሽን
 • በኢተዮ ቴሌኮም በተቀመጠው ኮሚስን መሰረት ተስማምቶ መስራት የሚችል፤
 • የኮሚሽኑ ምጣኔ በኢትዮ ቴሌኮም ሊቀየር ይችላል፡፡
 • ኢትዮ ቴሌኮም ሙሉ ኮሚሽኑን ለአከፋፋዩ ይከፍላል
 • አከፋፋዩ በተዋረድ ለሚገኙ በስሩ ላሉ ንዑስ አከፋፋዮች ኮሚሽን የመክፍል ኃላፊነት አለበት፡፡

ከላይ በተጠቀሰው መስፍርት መሰረት መስራት ከፈለጉ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ 6ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ዝቅ ብሎ በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ዞን ኢትዮ ትቴኮም ቢሮ በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0111243081/0911609988/0930377172

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives