የጨረታ ማስታወቂያ ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ፤ የዉሃ ማጣሪያዎችን፣ ፍሪጆችን፣ ቴሌቭዥኖችን ፤ ካዝናዎችን፤ እና ሌሎች ተመሳሳይ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ዐ4/2014

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ፤ የዉሃ ማጣሪያዎችን፣ ፍሪጆችን፣ ቴሌቭዥኖችን ፤ ካዝናዎችን፤ እና ሌሎች ተመሳሳይ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በቴሌ ብር አማካኝነት  የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል ከ www.extratenders.com እና www.afrotender.com ዌብ ሳይቶች  መግዛት የሚችሉ ሲሆን ንብረቶቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ መታወቂያቸውን በመያዝ  በመሰቀል ፍላወር የሚገኘው የድርጅቱ ዕቃ ግምጃ ቤት እና አቃቂ በሚገኙት የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች ማየት ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚዘጋው ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ነው፡፡የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቦታ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም እቃ ግምጃ ቤት፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ አቃቂ ከሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives