ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን የላቀ ፍጥነት ያለው የLTE Advanced አገልግሎት ጀመረ

የLTE Advanced አገልግሎት በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ከተሞች ማስጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ከመዲናችን አዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ውስጥ በሚገኙ ስድስት ከተሞች ማለትም በአዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ዱከም፣ ገላን፣ ሞጆ እና አዋሽ መልካሳ የLTE Advanced አገልግሎቱን ማስጀመር ተችሏል፡፡

የLTE Advanced አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው፡፡

በኩባንያችን የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ላይ እንደተመለከተው በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የ4G LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሠራ ሲሆን በዚህም መሠረት በቀጣይ ወራት በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ በመረጃ የበለጸገ ማኅበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም እንዲቻል የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና ይዘት (content) አቅራቢዎች የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለኅብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታበረክቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የካቲት 11 ቀን 2013 .

ኢትዮ ቴሌኮም

We are pleased to announce the launching of LTE advanced service in South East Region – for the first time outside of the capital, Addis Ababa.

The LTE expansion has covered towns: Adama, Bishoftu, Mojo, Dukem, Gelan and Awash Melkasa, where high mobile data traffic has been observed. Given the reliability, high bandwidth and high speed features of LTE Advanced services,

we hope that it will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences. We sincerely appreciate all our stakeholders who have provided required supports to realize the project within short period of time.

As clearly outlined in our three-years growth strategy, data traffic growth and demand based 4G/LTE expansion in Addis and regional towns is among the major strategic initiatives. Accordingly, over the next few months, we will be launching similar services in other parts of the country, for which preparation works are underway.

In this regard, we would like to call up on players in the ecosystem to capitalize this opportunity by providing useful contents & affordable handsets and join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.