ዑምራ የሮሚንግ ጥቅል

የዑምራ ሥነ ሥርዐትን ለማከናወን ለሚያመሩ ምእመናንና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ሳዑዲ ቅዱሳን ከተሞች ለሚያቀኑ ተጓዦች የተዘጋጀ፤ ልዩ የዑምራ ሮሚንግ ጥቅል በአማራጭ ከኢትዮ ቴሌኮም።

በመንፈሳዊም ሆነ በንግድ ለሚደረጉ ጉዞዎች፣ ግንኙነቶችን ሳይቋረጡ እንደ ነበሩ ለማስቀጠል፤ ከአገር ውስጥ ኔትዎርክ በተጨማሪ በሌሎች የኔትዎርክ መዳረሻዎች ለመገልገል፤ ለተለያዩ ዐላማዎች በዐይነት የቀረበ ጥቅል።

ዑምራ ጥቅል ዐይነት

ድምፅ + ዳታ

የቆይታ ጊዜ

የቀረበው ጥቅል

ዋጋ በብር

ለ 15ቀናት

500 ሜ.ባ + 75 ደቂቃ

2430.00

    1 ጊ.ባ + 150 ደቂቃ

4800.00

ድምፅ ብቻ

የቆይታ ጊዜ

የቀረበው ጥቅል

ዋጋ በብር

ለ 15 ቀናት

90 ደቂቃ

2100.00

ለ 30 ቀናት

180 ደቂቃ

4100.00

ዳታ ብቻ

የቆይታ ጊዜ

የቀረበው ጥቅል

ዋጋ በብር

ለ 15 ቀናት

1.5 ጊ.ባ

2100.00

ለ 30 ቀናት

3 ጊ.ባ

4100.00

ደንብና ኹኔታዎች

  1. ብቁነት
    • ይህንየሮሚንግ ጥቅል፤ የኢትዮ ቴሌኮምን ቅድመ ክፍያ፣ ድኅረ ክፍያና ሁለቱንም በጋራ የሚጠቀሙ የሞባይል ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
  1. አገልግሎት ወሰን
  • ይህ ጥቅልበሳዑዲ ዐረቢያ አገር ብቻ የሚወሰን ሲሆን፤ ከሳዑዲ ውጭ ባሉ አገራት የሚጠቀሙ ከሆነ በመደበኛ የሮሚንግ ጥቅል ታሪፍ ክፍያው የሚታሰብ ይሆናል።
  1.  የቆይታ ጊዜ
  • የጥቅልአማራጮች እንደ ተቀመጠላቸው የአገልግሎት ጊዜ ገደብ፤ ለ15 ቀናት ወይም 30 ቀናት ውስጥ ብቻ ይቆያሉ።
  • ከተቀመጠውጊዜ በላይ ጥቅሉ ካላለቀ ለ3 ቀናት ብቻ ተጨማሪ የቆይታ ጊዜ ያገኛሉ
  1. የጥቅአጠቃቀም
  • ጥቅሉበሚከተሉት አገልግሎቶች ላይ ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል፦
  • በውጪአገራት የኔትዎርክ መዳረሻ ዳታ ለመጠቀም፣
  • ወደ ኢትዮጵያ ጥሪዎችንለማድረግ፣
  • ጥሪዎችንለመቀበል፣
  • የዳታ አገልግሎት ለመጠቀም።
  1. የግዢ አማራጮች

ደንበኞች ጥቅሉን በሚከተሉት አማራጮች ማግኘት ይችላሉ፦

  • ኢትዮ ገበታ (999#)
  • Telebirr
  • CRM
  • My Ethiotel App
  • Chatbot
  1.  ተጨማሪግዢዎች
  • ደንበኞች በቅድሚያ የገዙት ጥቅልሳያልቅ ተጨማሪ የዑምራ ጥቅሎችን መግዛት ይችላል።
  • በአገር ውጭ ለሚገኙደንበኞች በtelebirr ወይም My Ethiotel መተግበሪያ የግዢ አማራጭ ጥቅሉን ማግኘት ይችላሉ።
  1. ከተፈቀደው ጥቅል በላይ ስላለው አጠቃቀም
  • ከተቀመጠው ጥቅል በላይ ለሆኑ አጠቃቀሞች፤ አሁን ባለው የሮሚንግ ታሪፍ መጠን መሠረት የሚከፈሉ ይሆናሉ።
  1. ማሳወቂያ
  • ደንበኞች በሚከተሉት ጉዳዮች የአጭርጽሑፍ መልእክት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል፦ 
  • ጥቅሉንየገዙበት ማሳወቂያ፣
  • 75% የተጠቀሙበትማሳወቂያና
  • ጥቅሉንበሙሉ የጨረሱበት ማሳወቂያ።

ማስታወሻ፦

  • ደንበኞች የዑምራን ጥቅሉ፤ ለራሳቸውምሆነ ለሌሎች ተጓዦች በስጦታ መላክ መግዛት ይቻላል።
  • ለሁሉም ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስና 15% ቫትን ያካተቱ ናቸው።