ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምሥራቅ ሪጅን የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምሥራቅ ሪጅን የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ  አገልግሎት ጀመረ::

ኩባንያችን በተለያዩ ሪጅኖች በሚገኙ 103 ከተሞች የ4G/LTE አገልግሎትን ለማስፋፋት የያዘውን ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ በዛሬው ዕለት በሰሜን ምሥራቅ ሪጅን የሚገኙ ሰባት ከተሞች ማለትም ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልዲያ፣ ሃይቅ ፣ ከሚሴ፣ ቆቦ፣ ላሊበላ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ   የሞባይል ኢንተርኔት  አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ያስችላቸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በሰሜን ምሥራቅ ሪጅን ተመርቆ በሥራ ላይ የዋለው የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት በከተሞቹ እየታየ ያለውን የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የተከናወነ ሲሆን ማስፋፊያው 577,000.00 በላይ የሚሆኑ በሪጅኑ ሥር የሚገኙ ደንበኞች በ4G LTE ሽፋን ውስጥ እንዲካተቱ አስችሏል፡፡

በቀጣይም ኩባንያችን በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ የ4G/LTE አገልግሎት ማስፋፊያ በማድረግ ለህብረተሰባችን በተከታታይ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰባችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

ኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን የተለያዩና የተቆራረጡ የፕላሰቲክ ነክ ማተሪያሎች፤የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ላሜራ ሽቶች፡ቱቦላሬ ብረቶች የኬብል ድራም ብረቶች ያገለገሉ የበርና መስኮቶች ፤አገልግሎት የሰጡ የታወር ብረቶች ፤ያገለገሉ የፌሮብረቶች ፤ የተነቀሉ የብረት በር እና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Read More »
Archives