ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው የሀገራችን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ መሠረት የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን በሚገኙ ስምንት ከተሞች (በደብረ ብርሃን፣ ፊቼ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ሱሉልታ፣ ሸኖ፣ ሰንዳፋ፣ ገርባ ጉራቻና ለገጣፎ) አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል።

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነታቸውን ለመጨመር እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ድረስ ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራዎች የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በ15 ሪጂኖች የሚገኙ 86 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል።

በቀጣይነትም ኩባንያው በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ እያከናወናቸው ያሉ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዚህ አጋጣሚ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በተስፋፋባቸው ከተሞች የምትገኙ ደንበኞች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያችን የሽያጭ ማዕከል የ3ጂ ሲም ካርዳችሁን ወደ 4ጂ በነፃ በማሳደግ 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ መጠቀም በሚያስችል የሞባይል ቀፎ፣ ታብሌት ወይም ዶንግል አማካኝነት እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንድትጠቀሙ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በተጨማሪም የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

         መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም

                ኢትዮ ቴሌኮም

Ethio telecom Launches 4G LTE Advanced Mobile Internet Service in Central North Region

Following its strategic plan to expand 4G LTE service in various cities of our country where there is high data usage, Ethio telecom has launched 4G LTE Advanced mobile internet service today on 23 September 2021 in the Central North Region (Debre Berhan, Fiche, Shewa Robit, Sululta, Sheno, Sendafa, Gerba Guracha and Legetafo) towns where high mobile data traffic has been observed. It is believed that high bandwidth, high-speed features and reliable data services of 4G LTE will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences.

Ethio telecom has so far expanded its 4G LTE service in 86 towns of 15 regions across the country and in Addis Ababa including Central North Region where 4G LTE service is launched today.  Likewise, our company is about to finalize the expansion of 4G LTE service in line with the data growth and demand and is in the process of launching the service in various regional towns soon.

In this regard, we would like to call up on players in the ecosystem to use this opportunity by providing useful contents & affordable handsets as well as to join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.

We are also pleased to request our esteemed customers who reside in those towns where the 4G LTE service is already launched and available to visit our nearby telecom shops and upgrade their 3G SIM cards to 4G for free of charge so as to enjoy the benefits of 4G LTE internet service.

           13 September 2021

                Ethio telecom

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives