ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው የሀገራችን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ለማስፋፋት በያዘው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ መሠረት የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በምዕራብ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ ከተሞች ማለትም በአሶሳ፣ ባምባሲ፣ ግልገል በለስ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል።

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነታቸውን ለመጨመር እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ሲያከናውን የቆየውን የመጀመሪያውን ዙር የ4 ኤል.. አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራ ማጠናቀቁን በደስታ እየገለጸ ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራዎች የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በ16 ሪጂኖች የሚገኙ 92 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል።

በቀጣይነት በሁለተኛው ዙር የኔትወርክ ማሳደግ እና ማስፋፊያ ስራዎችን ኩባንያው በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በማከናወን ላይ ሲሆን የማስፋፊያ ሥራዎቹ እንደተጠናቀቁ ለክቡራን ደንበኞቻችን የምናሳውቅ ይሆናል።

በዚህ አጋጣሚ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በተስፋፋባቸው ከተሞች የምትገኙ ደንበኞች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያችን የሽያጭ ማዕከል የ3ጂ ሲም ካርዳችሁን ወደ 4ጂ በነፃ በማሳደግ 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ መጠቀም በሚያስችል የሞባይል ቀፎ፣ ታብሌት ወይም ዶንግል አማካኝነት እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንድትጠቀሙ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በተጨማሪም የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

          መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም

                   ኢትዮ ቴሌኮም

Ethio telecom Launches 4G LTE Advanced Mobile Internet Service in West West Region

Following its strategic plan to expand 4G LTE service in various cities across the nation where there is high data usage, Ethio telecom has launched 4G LTE Advanced mobile internet service today on 30 September 2021 in the West West Region specifically Assosa, Bambasi, and Gilgel Beles towns including the Grand Ethiopian Renaissance Dam where high mobile data traffic has been observed. It is believed that high bandwidth, high-speed features and reliable data services of 4G LTE will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences.

We are thrilled to announce that phase-I 4G LTE service expansion which was planned for 2020/21 budget year is successfully completed by covering 92 towns in our 16 regions nationwide and in Addis Ababa including West West Region where 4G LTE service is launched today. Likewise, our company is immensely working on phase -II network upgrade and expansion in association with the ever-growing data demands and will announce for its esteemed customers as soon as the expansions are finalized.

In this regard, we would like to call up on players in the ecosystem to use this opportunity in providing useful contents & affordable handsets as well as to join hands in realizing digital inclusion in order to foster the need for digital economy.

We would also like to request our esteemed customers who dwell in those towns where the 4G LTE service is already launched and available to visit our nearby telecom shops and upgrade their 3G SIM cards to 4G for free of charge so as to enjoy the benefits of 4G LTE internet service.

           30 September 2021

                 Ethio telecom

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives