ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎች የደብተር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ለ2014 የትምህርት ዘመን በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ላላቸው ተማሪዎች 600,000 የመማሪያ ደብተሮች ድጋፍ አደረገ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም እንደ አንድ ሀገራዊ ተቋም የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ በዋናነትም የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ ጫና ለመጋራት፣ ተማሪዎች መሰረታዊ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው ለማድረግ፣ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ ለማስቻል፣ ነገ የተሻለ ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም ኩባንያው በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ የእድገት እንቅስቃሴ በመሳተፍ እና ሀገራዊ አለኝታነቱንና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተግባር ለማሳየት የትምህርት ዘርፉን እና ተማሪዎችን በትምህርት ግብዓት መደገፍ ሀገራዊ የትውልድ ግንባታ መጠነሰፊ እንቅስቃሴና ጥረት ለማገዝ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

የመማሪያ ደብተር ድጋፉ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ 666 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የመማሪያ ደብተር ድጋፉ የተደረገላቸው ተማሪዎችን እና ድጋፍ የተደረገላቸውን ት/ቤቶች በመምረጡ ሂደት የክልል የትምህርት ቢሮዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

ተ.ቁ ሪጅን የተማሪዎች ቁጥር የደብተር ብዛት
1 ምዕራብ ሪጅን (ነቀምቴ) 4,807 57,684
2 ማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን (አምቦ) 2,000 24,000
3 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጅን (ሰመራ) 1,500 18,000
4 ምስራቅ ምስራቅ ሪጅን (ጅግጅጋ) 2,000 24,000
5 ሰሜን ምዕራብ ሪጅን (ባሕር ዳር) 3,000 36,000
6 ማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን (ሐረር) 1,554 18,648
7 ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን (ደብረ ብርሃን) 2,744 32,928
8 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን (ጎንደር) 2,484 29,808
9 ደቡብ ሪጅን (ሐዋሳ) 4,481 53,772
10 ደቡብ ምስራቅ ሪጅን (አዳማ) 3,500 42,000
11 ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን (አሶሳ) 1,590 19,080
12 ምስራቅ ሪጅን (ድሬ ዳዋ) 2,500 30,000
13 ደቡብ ምዕራብ ሪጅን (ጅማ) 5,992 71,904
14 ሰሜን ምስራቅ ሪጅን (ደሴ) 5,369 64,428
15 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን (ጋምቤላ) 1,500 18,000
16 ሰሜን ሪጅን (መቐለ) 1,973 23,676
17 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን (ወላይታ) 3,006 36,072
   ጠቅላላ ድምር 50,000 600,000

ትምህርት ለአንድ ሀገር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የተማረ የሰው ኃይል የመልካም ማህበረሰብ መሠረትና የቀጣይ ሀገር ኢኮኖሚ ዋልታ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ርብርብ ለማሳካት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሶስት ዓመታት (ከ2011-2013 ዓ.ም) በትምህርት ዘርፉ በርካታ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን ለአብነትም፡-

 • በ13 የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚማሩ 840 ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ፣
 • በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 2,220 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ፣
 • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ አማራና ትግራይ ክልሎች ለትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ፣
 • ኩባንያው በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ 100 ሴቶች የሙያ ስልጠና የገንዘብ ድጋፍ፣
 • በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመላ ሀገሪቱ ሀገሪቱ በሚገኙ 93 መጀመሪያ ደረጃ ት/ት ለሚማሩ 32,974 ተማሪዎች 32,974 ደርዘን የመማሪያ ደብተር፣
 • ለ5,116 ተማሪዎች የደብተር ቦርሳና ዩኒፎርም ድጋፍ፣
 • በ7 ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 1,040 ተማሪዎችን ለማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ፣
 • ለትምህርት ሥርጭት (14.03 ሚሊዮን ብር) እና ለስኩል ኔት (45.62 ሚሊዮን ብር) የሚከፈሉ ክፍያዎች በድምሩ 59.65 ሚሊዮን ብር ቅናሽ ተደርጓል
 • 50 ላፕቶና 200 ዘመናዊ የስልክ ቀፎ በመላ ሀገሪቱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴት መምህራን ስጦታ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ለትምህርት ዘርፉ ከሚያደርገው ቀጥተኛ ተሳትፎ ባሻገር በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ለአብነትም ያህል በ2013 በጀት ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውል የ847.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከእነዚሀም መካከል፡

 • ለገበታ ለሀገር 500 ሚሊዮን ብር፣
 • ለመንግሥት ፕሮጀክቶች 177.91 ሚሊዮን ብር፣
 • ለኮቪድ-19 ድጋፍ 16 ሚሊዮን ብር፣
 • ለአጭር ቁጥርና በአጭር ቁጥር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት ለሚደረጉ ድጋፎች በድምሩ 92.23 ሚሊዮን ብር፣
 • ለማህበረሰብ እና ሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት 41.1 ሚሊዮን ብርና
 • ለአካባቢ ልማት አገልግሎት 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በአጠቃላይ ለደብተር ድጋፉ ከ16.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይም በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

                                               ኢትዮ ቴሌኮም

                                     መስከረም 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives