ወርኃዊ የቴሌኮም አገልግሎት ሂሳብ መክፈያ አማራጮች

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቀላል እና ምቹ አማራጮች በመጠቀም ወርኃዊ የቴሌኮም ገልግሎት ክፍያዎን በቀላሉ መፈጸም የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን፡፡

1. በአካል በመቅረብ
በአቅራቢያዎ በሚገኙ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆችና ሌሎች የንግድ ማዕላት
– በይሙሉ አገልግሎት፣
– በኤሌክትሮኒክ ቫውቸር ካርድ /ኢቪዲ/ እንዲሁም
– በቅድመ ክፍያ ሞባይል ካርድ አማካኝነት

2. በሞባይል ዋሌት
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ሲቢኢ ብር)፣ የአዋሽ ባንክ፣ የኅብረት ባንክ ወይም የሄሎ ካሽ ሞባይል ዋሌት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ ደግሞ ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ መክፈል ይችላሉ፡፡

3. በባንክ ተቀማጭ ሂሳብ

የድርጅት ደንበኛ ከሆኑ ከሽያጭ ማዕከሎቻችን በተጨማሪ አካውንትዎ ከሚገኝበት ባንክ በኩል በቀጥታ የባንክ ማዘዣ (Direct Debt Standing Order) መክፈል እንዲችሉ በአቅራቢያዎ በሚገኝ የሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ በተቋማችንና በባንኩ አማካኝነት የተዘጋጀውን የውል ስምምነት በመፈረም በቀላሉ መክፈል ይችላሉ::

4. በኢትዮ ቴሌኮም እና ፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከላት

በኢትዮ ቴሌኮም ወይም የፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከላት በአካል በመቅረብ በቀላሉ መክፈል የሚችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ የጫኑ