ኢትዮ ቴሌኮም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የአገልግሎት ማሻሻያ እና እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም  የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተለያዩ ማሻሻዎችን እና እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ኩባንያው የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል  ደንበኞቹ፣ አጋር ድርጅቶቹ እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ስነ-ስርዓት አስታውቋል፡፡ ኩባንያው መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማፋጠን ካለው ቁርጠኛ አቋም በመነሳት የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ ነድፎ ዘርፈ ብዙ...